መንግስት የፅንፈኛው ሕወሐት ቡድንን ለሕግ ለማቅረብ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ እንደሚደግፉ የድሬደዋ አስተዳደር ነዋሪዋች ገልፀዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር ነዋሪዋች መከላከያ ሰራዊት የጀመረውን የህግ የማስከበርና የህልውና ተልዕኮ አጠናክሮ እንዲቀጥል የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል። ሰልፈኞቹ በጠዋት የጁንታው ህወሓት ቡድን ሀሠተኛ ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም !! የከሀዲውና ፅንፈኛው ህወሓት ፀባጫሪነት መልካም ከሆነው የትግራይ ህዝብ አይነጥለንም!! ጁንታው የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ አንድነታችንና ብልፅግናችን አይነቀንቀንም!! የሚል መፈክሮችን ይዘው በመውጣት ከሐዲው የሕውሀት ቡድን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን የሽብር…


