የድሬደዋ አስተዳደር ነዋሪዋች መከላከያ ሰራዊት የጀመረውን የህግ የማስከበርና የህልውና ተልዕኮ አጠናክሮ እንዲቀጥል የድጋፍ ሰልፍ አድርገዋል።
ሰልፈኞቹ በጠዋት የጁንታው ህወሓት ቡድን ሀሠተኛ ፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም !!
የከሀዲውና ፅንፈኛው ህወሓት ፀባጫሪነት መልካም ከሆነው የትግራይ ህዝብ አይነጥለንም!!
ጁንታው የህወሓት ቡድን ከሃገራዊ አንድነታችንና ብልፅግናችን አይነቀንቀንም!! የሚል መፈክሮችን ይዘው በመውጣት ከሐዲው የሕውሀት ቡድን በሰሜን ዕዝ መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን የሽብር ተግባር አውግዘዋል።
የአስተዳደሩ ከንቲባ አህመድ መሀመድ ቡህ ሰልፍ በተዘጋጀበት በስቴድየም ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ከሀዲው የህውሀት ጁንታ ለፍርድ እሲኪቀርብ ድረስ አስተዳደሩና ነዋሪው ህብረተሰብ የፀና ድጋፋቸውን ያደርጋሉ ብለዋል።
ከንቲባው ከዚህም ጋር በማያያዝ ለ27 አመታት ሀገሪቷን ሲበዘብዝ የቆየው የጁንታው ቡድን በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ የፈፀመው ክህደት የእጁን እንዲያገኝ ሁሉም ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።


