በድሬዳዋ አስተዳደር በ2012 ግብር ዘመን ለተለዩ ታማኝና ከፍተኛ ግብር ከፋዮች የዕውቅና መድረክ ተካሄደ::
በሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብርና መስዋዕትነት የህሊና ጸሎትና በሃይማኖት አባቶች ምርቃት የተጀመረው የእውቅና መድረክ መርሃግብር መሰረት የእንኳን ደህና መጣችሁና መክፈቻ ንግግር በአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተጀምሯል። እንደ ድሬዳዋ የተጀመረው ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ተሸላሚዎች በእውቅናው ሳይዘናጉ ሌሎችንም በማበረታታት ወደዚህ ስርዓት እንዲቀላቀሉ ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ቃል በመግባት…


