በሀገር መከላከያ ሰራዊት ክብርና መስዋዕትነት የህሊና ጸሎትና በሃይማኖት አባቶች ምርቃት የተጀመረው የእውቅና መድረክ መርሃግብር መሰረት የእንኳን ደህና መጣችሁና መክፈቻ ንግግር በአስተዳደሩ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሀመድ ተጀምሯል።
እንደ ድሬዳዋ የተጀመረው ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ተሸላሚዎች በእውቅናው ሳይዘናጉ ሌሎችንም በማበረታታት ወደዚህ ስርዓት እንዲቀላቀሉ ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ቃል በመግባት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር ለተሸላሚዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ተሸላሚዎችን በተመለከተ ታማኝ ግብር ከፋዮች የተለዩበትን መስፈርትና ሂደቱ በሽልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ በአቶ ዋሲሁን አብርሃ በገለጻ ቀርቧል።
በሲሳይ ዘለገሀሬ ግጥም የታጀበው እውቅናና የምስጋና ሰርተፊኬት ሰነ ስርዓት 14 በሶስተኛ ደረጃ፣ 12 በሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም 4 በአንደኛ ደረጃ በአጠቃላይ ለ30 ተሸላሚዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
በተለያዩ ዘርፎች ለግብር አምባሳደሮች ቃል የመግባትና የፎቶ የመነሳት ስነስርዓት በማካሄድ በአቶ መሀመድ ኡሶ የፌደራል ገቢዎች ሚኒስቴር ተወካይ የማጠቃለያ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቅቋል።
በመድረኩ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የፓርቲና ካቢኔዎች፣ የሃይማኖትና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትና ተሸላሚዎች ተገኝተዋል።
ግብር እዳ አይደለም ከቆየ ግን እዳ መሆኑ አይቀርም
ግብርን በወቅቱ በመክፈል የሀገራችንን ብልጽግና እናረጋግጥ


