ከዛሬ አራት አመት በፊት ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባው የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የህብረተሰቡን የመሬት ይዞታ በማረጋገጥና በመመዝገብ በዘመናዊ መንገድ ወደ መረጃ ቋት በማስገባት ከዚህ ቀደም ይጠፍ የነበሩትን መረጃዎች የሚያስቀሩ አሰራሮችን በመስራት ላይ ይገኛል።
ኤጀንሲው እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች ነዋሪው ህብረተሰብ በቂ ግንዛቤ በመያዝ በቀጣይ ኤጀንሲው ለሚሰራቸው ስራዎች ትብብር ያደርግ ዘንድ በ 02 ቀበሌ ከሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂዷል ።
ኤጀንሲው ከተቋቋመ አራት አመት ቢሆነውም ነገር ግን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ በበቂ ሁኔታ እንዳልተሰራና አሁን ላይ ግን ኤጀንሲው እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች ለህብረተሰቡ በማስገነዘብ ላይ እንደሚገኝና ህብረተሰቡም ኤጀንሲው እያከናወናቸው ባሉት ስራዎች ደስተኛ እንደሆኑ
የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሙና መሀመድ ተናግረው ኤጀንሲው ለሚሰራቸው ስራዎች ግልፅነት ይኖረው ዘንድ ከህዝብ በተመረጡ አባላት ስራዎችን በመስራት የሚነሱ ቅሬታዎችም ካሉ ህዝቡ በመረጣቸው አካላት ፍፁም ግልፅነት በተሞላበት መልኩ ቅሬታዎቹ የሚፈቱ መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር ተናግርዋል ።
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የ 02 ቀበሌ ነዋሪዎች በበኩላቸው ከመሬት ጋር ተያይዞ መፈታት ያለባቸው የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲሁም ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ ነዋሪው ህብረተሰብ ያለውን ጥያቄ ለሚመለከታቸው የኤጀንሲው አመራሮች ጥያቄያቸውን በማቅረብና በጉዳዩ ላይም ውይይት በማካሄዳቸው መደሰታቸውን ተናግረው በቀጣይም ከነዋሪው ህብረተሰብ ጋር መሰል ውይይቶች መደረግ እንዳለባቸውም ተናግረዋል ።


