የአካል ብቃት እንቅስቃሴያችን ለሁለንተናዊ ጤናችን 2ኛው ከተማ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በርካታ የከተማው ነዋሪዎችን ባሳተፈ መልኩ በድሬዳዋ ምድር ባቡር አደባባይ ተካሂዷል፡፡
ከኮቪድ-19 ወረርሺኝ በህብረተሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን የጤና ችግር ለመቅረፍ አላማን አንግቦ የተጀመረው የድሬዳዋ ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በድሬዳዋ ምድር ባቡር አደባባይ በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄደ የ2ኛው ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትሜንት ቢ ኃላፊ አቶ ከዲር ጁሀር በዚህ…


