የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል የመሪ ቃል በአሰሊሶ ክላስተር ቦረን ቀበሌ 8ተኛው የተፋሰስ ልማት በታቀደው ቅዱ መሰረት በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ እየተከናወነ ይገኛል።
በአሰሊሶ ክላስተር ቦረን ቀበሌ እየተከናወነ ያለው የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ከተያዘው ጊዜ በፊት ማጠናቀቅ እንደሚችል ተሳታፊዎች ገልፀዋል ። በዚህ መሰረት በቀበሌው ይከናወናሉ ተብሎ የታቀዱ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች እንዲሁም የማሳ ውስጥ የእርሻ ስራዎች በተለመው መንገድ በከፍተኛ የህብረተሰብ ተሳትፎ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በካተተ መልኩ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።


