የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በጋራ በመሆን የሀገራችን ኢትዮጲያ ዋና ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ ላይ ተገንብተው ለህዝብ ክፍት የሆኑ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት ተደርጎባቸዋል ። በጉብኝቱ ላይም ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ ፣ የግብርና የታክስ አምባሳደሮች ፣ ባለድርሻ አካላት ፣ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል ።
ጉብኝቱ በተለይም በሀገራችን ኢትዮጲያ እየተሰሩ ያሉ እንዲሁም ተሰርተው ለህዝብ ይፋ የተደረጉ የልማት ስራዎች ከግብር ከፋዩች በሚሰበሰበው ገቢ እንደመሆኑ መጠን በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ታማኝ ግብር ከፋዮችና የታክስ አምባሳደሮች በሀገር ደረጃ እየተደረገ ያለውን ለውጥ በተግባር መተው እንዲያዩ በማድረግ በቀጣይ በሚደረገው የግብር ከፋይ ንቅናቄ ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዲያደርጉ ታስቦ የተዘጋጀ ጉብኝት ነው ።
ይህም ጉብኝት ሸገር ፕሮጀክት ፣ እንጦጦ ፓርክ እንዲሁም የአንድነት ፓርክ ጉብኝት የተደረገባቸው ሲሆን ጉብኝቱ ፍፁም የተሳካ ከመሆኑም ባለፈ ሀገራችን ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው ያሉትን የልማት ስራዎች በተጨባጭ በቦታው በመገኘት ማየታቸው ፍፁም እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም መሰል ፕሮጀክቶች ድሬዳዋ ላይ እንዲሰሩ የበኩላቸውን አስተዋፆ እንደሚወጡም ነው ጎብኚዎቹ የተናገሩት ።


