ለሠላም ለልማትና ለጋራ ተጠቃሚነት የያዝነው
የጸና አቋማችን ምን ጊዜም አሸናፊ ነው::
የበይ ተመልካች ሆነን ዘመናትያስቆጠርንበትን የአባይ ወንዝ ታሪክ ወደ አዲስ
ምዕራፍ ለመቀየር ማንንም ሳነጎዳ ለልማትየማዋል አቋማችን በምንም በማንም ሊቀለበስ
እንደማይችል ለሁሉም ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምን በተመለከተ የተዛቡ
አመለካከቶችና ከቅኝ ግዛት ጋር የተያያዙ አሠራሮች ባሉበት ሊቀጥሉ አይችሉም፡፡
በምንገኝት በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን በቅኝ ግዛት ወቅት የነበረን አመለካከትና አሠራር ይዞ
መቀጠል እንደማይቻል ለማንም ግልጽ ነው፡፡….ለበለጠ መረጃ ገፅ 3 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 2
ማህበራዊ ሚዲያ
ውድ አንባብያን ይህ ጽሁፌ ስለተመቸኝ አንብቡልኝ።በደንብ ይነበብ!!
የሰንበትረፋድ ምርጥ መረጃ! እንደምነህጌታዬ? እንዴትነሽእናቴ? የዚህ ሳምንት መረጃችን ደግሞ ይለያል! የፀዳነው! ይጠቅመናል አናንብበው፡፡
ጠዋት ስትነሳ ግራ እግርህ ይስራ አይስራ ሳታረጋግጥ መጀመርያ ስልክህን አንስተህ “facebook”
ቼክ ታደርጋለህ። ሽንት ቤት ቁጭ ብለህ “Instagram” ላይ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን “scroll”
እያደረክ ትኮሞኩማለህ። ስልክህ ካርድ ከሌለው ቶሎ ገዝተህ “ማህበራዊ ሚድያ” ላይ እስክትጣድ
ያንቀለቅልሃል! የሆነ ፅሁፍ ለጥፈህ ምን ያህል “like”
እና “comment” እንዳገኘህ ለማወቅ በየደቂቃው “Refresh” እያደረክ ታያለህ። የለጠፍሽው ፎቶ ምን
ያህል “like” እንዳገኘ ለማወቅ ያቅበዘብዝሻል። የጠበቅሽውን ያህል “Reaction” ካላገኘ ተበሳጭተሽ
ፎቶውን ታጠፊዋለሽ። “ማህበራዊ ሚድያ” ላይ የምታውቃቸው ሰዎች ለተወሰነ ግዜ ሲጠፉብህ
ይጨንቅሃል። ስማቸውን ሳይቀር ፅፈህ ትፈልጋቸዋለህ። ፎቶሽ ላይ ሁል ግዜ “…የኔ ቆንጆ፣
የኔ ልዕልት፣ ስታምሪ..” ምናምን እያለ “comment” የሚያደርግልሽ ልጅ በሆነ አጋጣሚ አዲስ የለጠፍሽው
ፎቶ ላይ “comment” ካላደረገ ያሳስብሻል። የለጠፍከው ፎቶ ወይም ፅሁፍ “like” ብዙም ካላገኘ
እራስህ “like” ታደርጋለህ። መስሪያ ቤትህ በሰጠህ ኮምፒውተር “facebook” ትጠቀማለህ።….. ለበለጠ መረጃ ገፅ 10 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 2
አድዋ የጥቁር ህዝብ ኩራት
ሀገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ስልጣኔና አኩሪ ታሪክ ባለቤት ናት፡፡በረጅም ዘመን ታሪኳ ጎልተው እና ደምቀው ከሚታወቁና ከሚታወሱ በርካታ የታሪክ ሁነቶች መካከል አንዱ የአድዋ ድልነው፡፡የአድዋ ድል የኢጣልያን ወራሪና ቅኝ ገዥ ኃይል ቅስም በመስበር የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ከመሆኑ ባሻገር በእኩይ የዘረኝነት መንፈስ ላይተ መስረቶ በመላው ዓለም የሚገኙ ጥቁር ሕዝቦችን በተለይም አፍሪካዉያንን በበታችነት ለዘላለም በቅኝ ለመግዛት አንደማይቻል አውሮፓውያንን ያስገነዘበ ዘመንተሻጋሪ ድል ነው፡፡….ለበለጠ መረጃ ገፅ 2 ያንብቡ መልዕክተ ድሬ7 1 2


