የትራንስፖርት ዘርፉ እንዲጠናከርና ውጤት እንዲያስመዘግብ ከተፈለገ ከሚዲያ አካላት እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ሊጠናከር ይገባል ተባለ፡፡
በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ የሚዲያ አካላት እና የሲቪክ ማህበራትን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት አሁን ላይ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ እያለቀ የሚገኘው ማህበረሰባችን አሃዝ በበሽታ እና ተያያዥ ምክንቶች እያለቀ ካለው ህብረተሰባችን ቁጥሩ ከፍ…


