የትራንስፖርት ዘርፉ እንዲጠናከርና ውጤት እንዲያስመዘግብ ከተፈለገ ከሚዲያ አካላት እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ሊጠናከር ይገባል ተባለ፡፡

    በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ የሚዲያ አካላት እና የሲቪክ ማህበራትን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በትራንስፖርት ሚኒስቴር እና ፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡
    መድረኩን በንግግር የከፈቱት የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት አሁን ላይ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ እያለቀ የሚገኘው ማህበረሰባችን አሃዝ በበሽታ እና ተያያዥ ምክንቶች እያለቀ ካለው ህብረተሰባችን ቁጥሩ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
    ይሁንና ለችግሩ የተሰጠው ትኩረት የአሳሳቢነቱን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
    በዚህ ረገድ የሚዲያ አካላትና የሲቪክ ማህበራት ማህበረሰቡን በማንቃት እንደሁም የችግሩን ስፋት በማስተጋባት እንዲንቀሳቀሱም ነው ዋና ዳይሬክተሯ ጥሪ ያቀረቡት፡፡
    የእለቱ መድረክ ዋና አላማም በቀጣይ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመፍታት ቅንጅታዊ ስራን በማጠናከር ውጤታማ ስራን ለመስራትም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
    ትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ጉልማ ታዬ አሁን ላይ እንደ ሀገር ብሎም እንደ አስተዳደር የትራፊክ አደጋ እያደረሰ ያለውን ተጽእኖ እና የሚዲያ አካላት እና የሲቪክ ማህበራት ድርሻን ያመላከተ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
    በጽሁፉ መነሻነትም የመድረኩ ተሳታፊ አካላትም መድረኩ መዘጋጀቱ በቀጣይ አብሮ ለመስራት መንገድ ሚከፍት መሆኑን ጠቁመው በተለይ በሚኒሰቴር መስሪያቤቱም ሆነ በትራስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየወሩ የሚደረጉ መርሀግብሮችን ከመዘገብ ባለፈ በቀጣይ የቀኝ ከቀን መረጃን ተቀናጅቶ ወደ ማህበረሰቡ ለማድረስ እንደሚሰሩ ለዚህም የሚዲያ ፎረም መቋም እንደሚገባው አስተያየት ሰተዋል፡፡የእምነት አባቶች በበኩላቸው በቤተእምነቶቻቸው ማህበረሰቡን በትራፊክ አደጋ አስከፊነት ለማስተማር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡