“የኢትዮጵያዊነት ቀን” እየተከበረ ነው::

    ዛሬ ጳጉሜ 1 ቀን 2013 ዓ.ም “የኢትዮጵያዊነት ቀን” በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ጀምሯል።
    ቀኑ “ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ” በሚል መርህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከፍ በማድረግ የሚከበር ቀን እንደሚሆን ይጠበቃል።
    ሰራተኛው በመሰሪያ ቤቱ ፣ ትራፊክ ፖሊስ በመንገዱ፤ አሽከርካሪው መኪናውን በማቆም፤ መላው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በያሉበት ለሁለት ደቂቃ “ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ “በሚል የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በማውለብለብ እና የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በመዘመር ኢትዮጵያን በማወደስ ቀኑን ያከብራሉ።