የድሬደዋ አስተዳደር አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በድሬደዋ ምክር ቤት የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ የምክር ቤት አባላት ዛሬ ጠዋት በምክር ቤት የመጨረሻ አጀንዳ የሆነውን የ2ኛ የስራ ዘመን 48ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ተወያይተው በማጽደቅ የስራ ዘመናቸው እንደሚጠናቀቅ በመግለፅ ለተሸኙ አባላትም የምስጋና ፕሮግራም እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡
አፈ ጉባኤዋ ከዚህም ጋር አያይዘው ምክር ቤቱ በዛሬ ከሰአት ውሎውም አዲስ ለሚገቡ የምክር ቤት አባላት የምክር ቤቱ ስነ-ምግባርና ደንብ የማስተዋወቅ እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
በነገው እለት ምክር ቤቱ በሚኖረው ጉባኤ የአስተዳደሩ አዲስ መንግስት ምስረታ እንደሚካሄድ አፈ ጉባኤዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል፡፡


