ትንሿ #ኢትዮጵያ የሁላችን #ድሬዳዋ ታመሠግናለች።

    በአስተዳደራችን አዘጋጅነት በውቧ የፍቅር ከተማችን ድሬዳዋ የተከበረው፤ የዘንድሮው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና፣ ህዝቦች ቀን በዓል በሠላምና በስኬት በመጠናቀቁ ተደስቻለሁ እንኳን ደስ አላችሁ።
    ይህ ስኬት የበርካታ ህብረ-ብሔራዊ ኢትዮጵያዊያን ጥረትና ድካም ድምር ውጤት ነው። ለዚህ ታላቅ ስኬት ኀላፊነታችሁን የተወጣችሁ፤ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የድሬዳዋ ፖሊስና ትራፊክ አባላት፤ በጎ-ፈቃደኛ ወጣቶች፤ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች፤ የወጣት አደረጃጀቶች፤ በየደረጃው የምትገኙ የሴክተር መስሪያ ቤትና የቀበሌ ፅ/ቤት አመራርና ሰራተኞች፤ ከሁሉ በላይ፣ ሰላም ወዳድና በፍቅር እንግዳ ተቀባይ የሆናችሁ የድሬዳዋ ነዋሪዎች፤ በአጠቃላይ በስም ያልጠቀስኳችሁና በልዩ-ልዩ መስክ በመሳተፍ የድርሻችሁን ጠጠር የወረወራችሁ፤ ውድ የድሬ ወዳጆች በሙሉ ለእናንተ ምስጋና ያንስባችኋል፤ አክብሮቴ ዘወትር ከልቤ ነው።