16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን እየተከበረ ነው

    16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ነው።
    “ወንድማማችነት ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ በሚገኘው 16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ላይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ተሳታፊ ሆነዋል።
    የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ህይወታቸው ላለፈ በህሊና ፀሎት በማድረግ እና በሀይማኖት አባቶች ምርቃት በዓሉ መከበር ጀምሯል።