ለአራት ተከታታይ ቀናት ለአስተዳደሩ አመራሮች በድህረ ጦርነት ስትራቴጂ ዙሪያ በየደረጃው ያሉ አመራሮች የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተጠናቋል።
ተገደን የገባንበት የህልውና ጦርነት የመጀመሪያ ምዕራፍ በድል በተጠናቀቀው የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ከሁሉም አመራሮች የሚጠበቅ ዋነኛ ተግባር መሆኑን እንዲሁም የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃትና በጥራት መፍታት እንደሚገባ ተገልጿል።
አገራዊ አንድነት ተናቦና ተቀናጅቶ የመስራት ልምድ ለጋራ ዓላማ በጋራ የመስራት ልምድ የአመራር ሁለንተናዊ ተሳትፎና ቁርጠኝነት ለአገራችን ዘላቂ ብልፅግና የመምራት አስፈላጊነት ላይ አመራሩ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ይሆናል፡፡
በቀጣይም ተመሳሳይ ስልጠናና ውይይቶች የተለያዩ አደረጃጀቶች፣ የመንግስት ሠራተኞች እና አጠቃላይ ህዝቡ የሚሳተፉበት መድረክ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል::


