ከ04,05 እና 06 መንደሮች የተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች በህወሃት አሸባሪ ሃይል ሀገር ለማፍረስ በከፈቱት ትግል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም መሀመድ፣ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቡሩክ ፈላቃ እና የድሬ ደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ ሲሆን ህዝቡ በአንድነት በመቆም የአካባቢያቸውን ደህንነትና ሰላም ለመጠበቅ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
ጠላቶቻችን በተለያዩ ሚዲያዎች በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ልጆቻችን፣ ጎረቤቶቻችንና ወንድሞቻችን እንዳይደናገጡ፣ ክልላችን በዘርና በሃይማኖት፣ በመንደርና በጎሣ እንዳይከፋፈል ተግተን እንሰራለን ፤ በምንችለውም ሁሉ ሁላችንም ከመንግስታችና ከመከላከያችን ጎን እንቆማለን ብሏል።
በተጨማሪም የውይይቱ ተሳታፊዎች በመንግስት የቀረበውን የሰላም ድርድር ትተው እንደ አሜሪካ ካሉ ጠላቶቻችን ጋር በመሆን በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ በከፈተው የግድያ ዘመቻ እና በሰሞኑ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በጋራ ካየነው ትዕግስታችን ከልክ አልፏልና ከአሁን በኋላ ከመንግስታችን ጎን በመሆን ፣ደም በመለገስ ፣አካባቢያችንን በመጠበቅ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ እና በንቃት በመጠበቅ እንዲሁም በመዝመት ሀገራችንን ከአደጋ ለመታደግ ሁሉም የበኩላችንን ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል ።
አሁን ህወሃት የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ነው ።ግን ህዝብን የማሸነፍ ስልጣን የላቸውም። እና በዚህ አንታለልም፤ ስለሆነም የድሬዳዋ ህዝብ እንደከዚህ ቀደሙ ምግብና መሳሪያ አዘጋጅተን በማቀበል የመጣውን ለውጥ በመደገፍ በህዝባችን ዘንድ ውዥንብር ለመፍጠር እየተሰራ ያለውን ፕሮፓጋንዳ አውቀን በጥንቃቄ እየተረዳን አገራችንን እንታድግ ብሏል።
አቶ አብዱልሰላም የአቡቲ እኩይ ሃይሎች ከጠላቶቻችን ጋር በጋራ በመሆን ሀገር ለማፍረስ የሚያደርጉትን ሴራ እና ጥቃት ልንከላከል ይገባል ብለዋል።
የሀገሪቱን ነፃነትና የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ መንግስት በተለያዩ መንገዶች የሀገሪቱን ዜጎች በማደራጀት በጠላቶቻችን ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው እናንተም አካባቢያችሁን ከፀጥታ አካላት ጋር ሆናችሁ እየጠብቃችሁ እንድትተባበሩና እንድታስተባብሩ ሲል መልዕክት አስተላልፏል።
አቶ ብሩክ ፈለቀ በበኩላቸውም ከአሁን በኋላ ህዝባችን በተለይም ወጣቶቻችን በአንድነት በመቆም አካባቢያቸውን ሊጠብቁ ይገባል ብሏል።
በሌላ በኩል እርስ በርስ መደጋገፍና በግብይት ውስጥም ቢሆን በመተሳሰብ አንድነታችሁን በመፍጠርና በማጠናከር ኢንዲሁም ላገራችን ሉኣላዊነትና ህልውና ለመጠበቅ ሲሉ ቤተሰብ ፥ሀብትና ንብረት ለቀው ወደ ግንባ የሄዱትን የጀግኖቻችን ቤተሰብ መንከባከብና መጠብቅ የሁላችንም ሀግራዊ ግዴታ ንው ብለዋል።
በኤልያስ አሜ
ፎቶ ፡የሙሉአለም ዳሴ


