የሃይማኖት አባቶች ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የሃይማኖት አባቶቹ የ2015 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡ በመልዕክታቸውም÷ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የፍቅር እና የትህትና መሠረት በመሆኑ ክርስቲያን ምዕመኑ ርስበርስ በመፋቀር እና በመዋደድ በተግባር ሊተረጉመው ይገባል ሲሉ የሃይማኖት አባቶች አሳስበዋል፡፡ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ወደዚች ምድር መምጣቱ ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅር ማሳያ በመሆኑ እኛም እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያሳየውን ፍቅር ማሳየት…


