የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲራዘም ወሰነ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 6/2015 ለመቀበልና ለማፅደቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1299/2015 ለማራዘም የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡን ረቂቅ ያቀረቡት የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በአዋጁ መራዘም አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ ማቅረባቸውን ተከትሎ የምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም ምክር ቤቱ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 5/2016 ሆኖ በ ሁለት ተቃውሞ፣ በሦስት ድምፀ ታዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲራዘም አፅድቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መራዘም ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የሥራ ዘመንን ለማራዘም የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ የውሳኔ ቁጥር 6/2016 ሆኖ በ2 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።


