የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን የተለያዩ አዋጆችን እና ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቋል

በትላንትናው እለት የተጀመረው ጉባኤ በዛሬው እለትም የቀጠለ ሲሆን

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር የአስፈፃሚው እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የግማሽ በጀት ዓመት ባቀረቡት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የምክር ቤቱ አባላት አስተያየት እና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ፤የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ በአስተዳደሩ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የቀረበለትን የተለያዩ አስፈፃሚ አካላትና ልዩ ልዩ ሹመቶችን አጽድቋል።

በዚህም መሰረት ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በመቀጠልም የተከበሩ ከንቲባ ለይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኝነት አቶ ሌሊሴ አሊይ፣ አቶ ጀማል ዩኒስ፣ አቶ አዋሌ ኢልሚ፣አቶ ፋህሚ አብዶንና አቶ አባይነህ ሙላቱን በእጩነት ቀርበው በሙሉ ድምጽ ጸድቋል።

የምክር ቤቱ ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባልነት አቶ አደም አሊ፣ አቶ ጀማል አብዲ፣ ወ/ሮ ኡመልኸይር ሙሴንና አቶ አብዲ ሀሰንን በእጩነት አቅርበው ሹመታቸው በሙሉ ድምፅ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *