የኢፌድሪ ማዕድን ሚኒስተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በወረዳ 9 አስተዳደር ስር እየተከናወኑ የሚገኙ የሌማት ቱሩፋት እንዲሁም የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን ጎበኙ

በዚህም የወረዳ 9 አስተዳደር በ 5 ወራቶች ውስጥ በአካባቢ ፅዳትና ውበት፣ በስራ እድል ፈጠራ ፣ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንዲሁም በሌማት ቱሩፋትና በሌሎችም ዘርፎች ያከናወናቸው ስራዎች ላይ ለእንግዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን፤ በመስክም በልብስ ሽያጭ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶችን በተጨማሪም በሌማት ቱሩፋት ስራም የማር ምርትን እንግዶች ተመልክተዋል።

እንግዶች ቀጥለውም የከተማ ስራ አስኪያጅ G+5 የህንፃ ግንባታ ፕሮጀክትን እንዲሁም የድሬዳዋን የኮሪደር ልማት የስራ እንቅስቃሴን በመዘዋወር ጎብኝተዋል።

የጉብኝት መርሀ-ግብሩ ነገም ቀጥሎ ይውላል።

ኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *