በሚካሔደው የኮሪደር ልማት ጎዳና ላይ የሚጣል የማህበረሰብ ክፍል የለንም ፦ ከንቲባ ከድር ጁሀር
#DGC መስከረም 20/2017 በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 03 አካባቢ የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር አወያይተዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የወረዳ 03 የልማት ተነሺዎች ጥያቄዎቻቸውን ለከንቲባ ከድር ጁሀር አቅርበዋል፤ ድሬዳዋ ከተማ በልማት ወደኋላ ቀርታለች መልማት አለባት ፤ ልማቷ ግን ህብረተሰቧን ሊጎዳና ጎዳና ሊጥል በሚችል መልኩ መሆን የለበትም ፤ በልማቱ ምክንያት እንድንነሳ የተሰጠን…


