እንኳን ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡
እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡ የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ…


