በድሬዳዋ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድር በመስቀለኛ ክለብ ሻምፒዮንነት ተጠናቀቀ።

ላለፉት አራት ወራት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም ከፍተኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ክለቦች ሻንፒዮና ውድድር በዛሬው ዕለት የፍፃሜ ጨዋታ መስቀለኛን ከ 06 ህብረት በኮንጎ ሜዳ ያገናኘ ሲሆን በመስቀለኛ አሸናፊነት ውድድሩ ተጠናቋል።

በዚህ ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከውድድሩ መጀመሪያ አስከ መዝጊያው ድረስ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ክትትልና ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የዛሬውንም የመዝጊያ የዋንጫ ግጥሚያንም ክቡር ከንቲባው ተከታትለዋል፤ ለአሸናፊውም ዋንጫውን አበርክተዋል።

በውድድሩ መዝጊያ ስነ-ስርአት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮምሽነር አለሙ መገራ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ፍራኦል ቡልቻ እንዲሁም የመስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች ተገኝተዋል።

በውድድሩ በርከት ያሉ የማበረታቻ ሽልማቶች በተለያዩ ዘርፎች ተበርክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *