በክህሎትና በተግባር የዳበረ ስራ ፈጣሪ ብቁ ዜጋ የማፍራት ስራ እየተከናወነ ነው” የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

ኮሌጅን በቴክኖሎጂ በማዘመን ጥራት ያለው ትምህርት እና ስልጠና በመስጠት የፈጠራ ክህሎት ያለው የሰለጠነ ዜጋ በማፍራት በኩል በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ሲሉ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሰልሀዲን አብዱልሃሚድ ገለጹ።

የኮሌጁ ዲን ይሀን ያሉት የዘርፉን ዕቅድ ለማሳካት የተሰሩ ስራዎችና በተገኙ ውጤቶች ዙሪያ የኮሙኒኬሽን ና የህዝብ ግንኙነት አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነዉ ።

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ በ12 የትምህርት ዘርፎች እንዲሁም በአጫጭር ስልጠና በ45 ዘርፎች በተለያዩ ደረጃዎች እያሰለጠነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዘንድሮ አመትም 10 ሺ ተማሪዎችን በአጫጭር ስልጠናዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ሙሉ ዝግጅቶችን አጠናቆ ወደ ስራ የገባ መሆኑን አቶ ሰላዲን ገልጸዋል።

በተያዘው አመትም ለገጠር ተማሪዎች እንዲሁም በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች የዶርሚተሪ አገልግሎቶችን ጭምር ለመስጠት የሚያስችል ስራዎችም መጠናቁቅንም አስረድተዋል።

ሰልጣኞች በእውቀት፣በክህሎትና በአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት ስራ ፈጣሪ እና የኢንድስትሪ አንቀሳቃሽ በመሆን ለሀገር ና ለህዝብ የሚጠቅም ዜጋን በመፍጠር፤ ኮሌጁ በግብዓት የሰለጠነ የሰው ሀይል በማደራጀት በኩል ከፍተኛ ጥረት ማድረጉንም አብራርተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀም በበኩላቸው ኮሌጁን በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማእከል ለማድረግም ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው አክለውም የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ስራዎች አተገባበር ውጤታማ ለማድረግ የመገናኛ ብዙሀንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

በመርሀግብሩ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በኮሌጁ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ክፍሎችንና ማሰልጠኛ ወርክሾፖችን ጎብኝተዋ፡፡

በሰላም ለማ

ምስል:- ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *