የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ 2017በጀት አመት የ 6ወር ስራ አፈፃፀምን አስመልክቶ በዋሂል ክላስተር በመገኘት የመስክ ምልከታ አድርጓል።
በዚህም ከክላስተሩ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት የክላስተሩን የ6ወር እቅድ አፈጻጸም፣ የሰላምና የጸጥታ ስራዎች ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ሰው ተኮር በሆኑ ጉዳዮች ላይ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ማለትም የአቅመ ደካሞች የቤት እድሳት፣ በደም ልገሳ የተሰሩ ስራዎችን፤ እንዲሁም ከአጎራባች ክልሎችና ክላስተሮች ጋር ስለሚሰራው ቅንጅታዊ ስራዎች እና በአጠቃላይም መሰል ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኡመር አህመድ በሰጡት የማጠቃለያ አቅጣጫም በእቅድና ሪፖርት በኩል ጥሩ ስራ መሰራቱን ገልጸው፤ ፖሊስ ጣቢያዎችም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀናጅተው እየሰሩ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የተከበሩ አቶ ኡመር አያይዘውም በቀጣይ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታነዩ ወጣ ገባዎች እንዲስተካከሉ አቅጣጫ ሰተዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-ሙሉዓለም ደሴ


