በመጽሃፉ ምረቃ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር “ቃቄ ከኢንሳ “ በሚል ርእስ ለአንባቢያን የቀረበው ይህ መጽፍ በወቅቱ አፍረን ቀሎ የባህል ቡድን በሚል የሽፋን ስያሜ የተመሰረተው ቡድን ኦሮሞዎች ብቻ ሳይሆኑ የሶማሌ ወንሞችና ሌሎች ብሔር ብሔረሶችንም ጭም በአንድነት በማሰባሰብ የወቅቱን ጭቆና ኪነትን እንደማታገያ ስልት በመጠቀም ለመታገል የተሰባሰቡትን የትግል ታሪክና ታጋዮች ታሪክ “ ማን ያርዳ የቀበረ ፣ ማን ያውጋ የነበረ” እንዲሉ ከምስረታው ጀምሮ የስብስቡ መሪ በነበረው ኢስማኤል መሃመድ ተሰንዶ መቅረቡ የመጽኃፉን ፋይዳ ያጎላዋል ብለዋል ፡፡
ከንቲባ ከድር ጁሀር በምረቃ ስነስርዓት መድረኩ ላይ በተለይም ይህ መጽፍ የወቅቱን የድሬዳዋ የኪነጥበብ፣ የፖለቲካና የባህል ማእከልነትታሪክ ጭምር የሚያወሳ በሆኑ ስለድሬዳዋ ከተጻፉ የታሪክ መጽሃፍት ውስጥ አንዱና ዋኛው ነው ሊባል ይችላል ነው ያሉት ፡፡
በአንድ መቶ ሰማኒያ ገጾች አምሳ አምስት የተለያዩ ንኡሳን ርእሶች የተዋቀረው ይህ “ቃንቄ ከኢንሳ “ በሚል ርእስ የተጻፈው የታሪክ መጽፍ ለአጥኒዎችና ተመራማሪዎች መነሻ.፣ ለጸሃፍትም የታሪክ ማጣቀሻ ሆኖ የሚያገልግል ከመሆኑም በላይ የአፋን ኦረቶሞ ቋንቋ ፖለቲካዊና የኪነጥበብ የሙያ ቃላት ፍቺ መዝገበ ቃላት ጭምር ነው ያሉት በአምቦ ዩኑቨርሲ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መምህር አሊዪ አብዱረህማን ናቸው፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የድዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፈቲያ ኤደን ፣ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የብልጽና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊና የመንግስት ተወካይ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ን ጨምሮ ከፍተኛ የእተዳደሩ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች እና ጥ ተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ደማቅ ስነ ስርዓት ተከናውኗል፡፡
ደራሲው ኢስማኤል መሐመድ ከሃምሳ ሰባት ዓመታት የውጭ ሀገር የስደት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን በዚሁ የመጽፍ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ከሃምሳ ዓመታት የውጭ ስደት ቆይታ በኋላ ወደሀገር የተመለሱት አብዱረህማን ባሬንቱን ጨምሮ አርቲሰት ሸንተም ሹቢሳ ፣ አርቲስ መሃመድ ሼካ ፣የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የክብር ዶክተር ጋዜጠኛና ደራሲ መሃመድ አህመድ ቆጴ አባ ገዳ አብረህማን የሃገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣት አማተር የኪነጥበብ ቡድኖችና አባላቶቻቸው የታደሙ ሲሆን ደራሲው በስ ስረዓቱ ላይ የተገኙ አካት ለመጽፉ መርቃት አዘጋጆችና ለመጽሃፉ ህትመት ሲስሩ የቆዩ ኮሚቴዎችን አመስግነዋል ፡፡
በዳንኤል አማረ
ፎቶ፦አገኘሁ ሸዋረጋ


