በኢትዮጲያ የቻይና አንባሳደር ቼን ሀይ የተመራ የህክምና ቡድን ለድል ጮራ ሆስፒታል ለድንገተኛ ህክምና የሚውሉ መዳኒቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

ልኡክ ቡድኑ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆንም የድል ጮራ ሆስፒታልን ጎብኝቷል።

በዚህም በመርሀ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተበረከተው ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ በበኩላቸው ድጋፉ ለሆስፒታሉ ተገልጋዮች ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ጠቁመው፤ በቀጣይም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን በማጠናከር አብሮ የመስራቱና የመደጋገፉ ሂደት እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

አንባሳደር ቼን ሀይ ድሬዳዋ የንግድ፣ የኢንደደስትሪና የኢንቨስትመንት ማእከል መሆኗን ገልፀው፤ በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍ የሁለቱ ሀገራትን ግንኙት እንደሚያጠናክረው ጠቁመዋል።

የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተርና የማህፀንና ፅንስ ሀኪም የሆኑት ዶ/ር በረከት ገብሩ በበኩላቸው የድል ጮራ ሆስፒታል ከድሬዳዋ ነዋሪዎች በተጨማሪም ለአጎራባች ክልሎች ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ የዛሬው ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው አብራርተዋል።

በጉብኝቱም ልኡክ ቡድኑ በሆስፒታሉ በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ታካሚዎችን እየተዘዋወረ በመጎብኘትና እሚያስፈልጋቸውን እርዳታና ሞያዊ ምክር ከተቋሙ ባለሞያዎች ጋር በመነጋገር ድጋፍ ማድረጉ ለእውቀት ሽግግር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ዶ/ር በረከት ጠቁመዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:-ሰላም አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *