“እናትና አባቴን ለመደገፍ እሮጣለው” በሚል መሪ ሀሳብ ለ9ኛ ጊዜ የዳዊት አረጋዊያን መርጃ ማዕከልከአስተዳደሩ የወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሩጫ ውድድር ተካሄደ።
መነሻውን እና መድረሻውን ምድር ባቡር ያደረገው የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በየ ዓመቱ አረጋውያኑን ለመደገፍ አላማ ያደረገ ሲሆን የዘንድሮ ውድድርም በቅርቡ ሂወቱን ላጣው እንድሁም ለበርካታ አመታት ይህን መርጃ ሲረዳ ለቆየው ለዶክተር አቤል መልካሙ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ታስቦም የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፕሮግራሙ አረጋውያኑን ከመደገፍም ባለፈ መታሰቢያነቱ ለዶክተር አቤል ፍቅር ለመግለፅ የተዘጋጀ መርሃ ግብር እንደሆነና በቀጣይም በዳዊት አረጋውያን መርጃ ማዕከል ያለውን ሃላፊነት እንደሚያስቀጥሉ ተናግረዋል።
በሩጫ ውድድሩም በሁሉም ውድድሮች አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል በተጨማሪም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የእውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ለዶክተር አቤል ቤተሰቦች የእውቅናና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል። ከዚህ በተጨማሪም ለምክር ቤት ዋንጫ ተበርክቷል።
በሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


