በድሬዳዋ አስተዳደር “እናት እና አባታችንን ለመደገፍ እንሩጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ታዋቂ አትሌቶች እና በርካታ ህብረተሰብ የተሳተፉበት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እየተካሄደ ነዉ።
ዳዊት አረጋውያን መርጃ ማዕከል ከወጣቶች ና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ የሩጫ ውድድር ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈትያ አደን እና በርካታ የከተማው ነዋሪዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶች እና አትሌቶች እየተሳተፉ ነዉ።
የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሩ ዓላማ በዋናነት አቅመ ደካማ አረጋውያን ለመንከባከብ እና ለመደገፍ እንደሆነ ተገልጿል ።
በሰላም ለማ
ምስል:- አገኘው ሸዋረጋ


