በዚህም በምርቃት መርሀ-ግብሩ የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በድኦ በመገኘት ቤት ለተገነባላቸው ወገኖች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ አቅመ ደካማ የሆኑ ወገኖችን በማገዝ እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን ማዳበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ቤቶቹ ተገንብተው እንዲጠናቀቁ ትብብርና ድጋፍ ላደረገው የድሬዳዋ አስተዳደርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን በበኩላቸው በዛሬው የቤት ምረቃ መርሀ-ግብር በገንደ ቆሬ ሳይት 5 ቤቶች እንዲሁም በመልካ ሳይት ደግሞ 4 ቤቶች በጠቅላላ 9 ቤቶች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ወቶበት እንደተገነባ ጠቁመው ፤ ለቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን ለማሟላትም ከ 2 መቶ ሺ ብር በላይ ወጪ መደረጉን አያይዘው ተናግረዋል።
ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለድሬዳዋ እያደረገ ለሚገኘው ሁሉን አቀፍ ድጋፍም አመስግነዋል።
ቤት የተገነባላቸው ወገኖች በበኩላቸው ከዚህ ቀደም በፈራረሰና ዝናብና ብርድ በሚያስገባ ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበረ ገልፀው፤ አሁን ላይ ቤታቸው ባማረ መልኩ ስለተሰራላቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:-አገኘሁ ሸዋረጋ


