በድሬዳዋ እየተሰሩ ላሉት የልማት ስራዎች ቻይና ድጋፍ እንደምታደርግ ተገለፀ

በኢትዮጲያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ መግባቱ ይታወቃል ። ልኡካን በድኑም ወደ ድሬዳዋ የመጡበት ዋንኛ አላማም የሁለቱ ሀገራትን ግንኙነት ለማጠናከር ሲሆን በድሬዳዋ በነበራቸው ቆይታም ለድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ለድንገተኛ ህክምና የሚውሉ መዳኒቶች እንዲሁም የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረግም ችለዋል ።

በኢትዮጲያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ የተመራ ልኡካን ቡድንም በዛሬው እለት ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል ። ኢትዮጲያ እና ቻይና ከ 55 አመት በላይ የቆየ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በተለይም በቴክኖሎጂ ፣ በባቡር ፣ በኮንስትራክሽን እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ዘሪያ በጋራ እየተሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክብር አቶ ከድር ጁሀር ተናግረው በአምባሳደሩ የተማራው የልኡካን ቡድንም በአስተዳደሩ ላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረጋቸውም በላይ በትምህርቱም መስክ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ሲያደረጉ እንደነበርና አሁንም ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የተናገሩት ።

በውይይቱ ላይም ስለ ድሬዳዋ አጠቃላይ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ባቡር ፣ በህክምና ፣ በቴክኖሎጂ ፣ በጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ኢንሸስትመንትን ጨምሮ በቀጣይ በተለያዩ መስኮች በጋራ ከመስራት ባለፈ ለአስተዳደሩም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ነው በኢትዮጲያ የቻይና አምባሳደር የሆኑት ቼን ሀይ ያስታወቁት ።

በአለማየሁ አበበ

ፎቶ:- ረመዳን አደም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *