ሄር ኢሴ” የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስነ-ስርዓት በዩኒስኮ መመዝገቡን ተከትሎ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ አካሄደ
በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባ አደም የሄር ኢሴ የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ያልተፃፈ ባህላዊ ህግ በሰው ልጆች ወካይ አለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስነት በመመዝገቡ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ኡባ አያይዘውም የማንነታችን መገለጫ የሆኑ የራሳችንን ባህሎች ማደበር እንደሚገባ ተናግረው፤ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲም እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንደሚገን ገልፀዋል፤ በቀጣይም በሄር…


