የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተልዕኮውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል – ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አየር ኃይሉ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እና የግዳጅ አፈፃፀም እንቅስቃሴዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል በየዘመናቱ ሁሉ የተሰጡትን ሃገራዊ ግዳጅ እና ተልዕኮዎችን በአስተማማኝ ብቃት እተወጣ ዛሬ ላይ የደረሰ በድል እና በመስዋዕትነት የደመቀ አኩሪ ታሪክ ያለው አንጋፋና ስመ ገናና የአቭዬሽን ተቋሙ ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ አሁንም ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተደራጅቶ የኢትዮጵያን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ ዘመናዊ የስልጠና ሂደትን በመከተል ብቃት ያላቸው ተተኪ ባለሙያዎችን ለማፍራት ትኩረቱን የአየር ኃይል አካዳሚ ላይ በማድረግ የዘመኑን የአቭዬሽን ቴክኖሎጂ መጠቀም የሚችሉ በርካታ ባለሙያዎችን እያፈራ የሚገኝ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ምንጭ፡ Etv News Amharic ኢቲቪ ዜና አማሪክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *