በድሬዳዋ እየተካሔደ ባለው የድሬ ሀሪፍ ሀገር አቀፍ የሳይክል ሻምፒዮና በሁለተኛው ዙር ውድድር የወልዋሎ አዲግራት አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ ተወዳዳሪው ኃይለመለኮት ወልደ አብእዝጊ አንደኛ በመውጣት አጠናቅቋል

#DGC ታህሳስ 29/2017

የሁለተኛው ዙር ውድድር በድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ፊትለፊት መነሻና መድረሻውን አድርጎ በ29 ዙሮች የአንድ መቶ ኪ/ሜትር እርቀት የሸፈነ ሲሆን ከስድስት የብስክሌት ክለቦች የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች ጠንካራ ፉክከር አድርገውበታል ፡፡

በውድድሩ አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው ኃለመለኮት ወልደ አብእዝጊ ስለውድድሩ በሰጠው አስተያየት ጠናካራ ፊክክር የተደረገበት መሆኑን ጠቅሶ በተለይ የድሬዳዋ ብስክሌት አፍቃሪው ተመልካች ለስፖርቱ ያለው የተለየ ፍቅር ለተወዳዳሪዎችም ልዩ ሞራል የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር የሳይክል ስፖርት እንዲጠናከር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሌሎችም በአርዓያነት የሚጠቀስ ያለው የኃይለመለኮት በዛሬው ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ተወዳዳሪዎችን በመተር ሳይክል ከፊት እየመሩ ውድድሩን መምራታቸው ልዩ ስሜት የሚሰጥና የድሬዳዋን የሰላም ከተማነት ማሳያ ነው ብሏል።

በቅርቡ የተቋቋመው ቶቶ የሳይክል ክለብ ተወዳዳሪው አሚር ጃፋር ውድድሩን ሁለተኛ ሆኖ አጠናቅቋል ፡፡ አሚር በውድድሩ ማጠናቀቂያ ላይ በሠጠው አስተያየት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሐር የሁለተኛውን ዙር ውድድር በሞተር አጅበው መምራታቸው ለተወዳዳሪዎች ልዩ ሞራል የሚሰጥ መሆኑን አንስቶ ስፖርቱን በመደገፍ ረገድ በአርዓያነት የሚነሱ ናቸው ብሏል ፡፡

አሚር የቶቶ የሳይክል ክለብን ከመመስረት አንስተው ይህ ውድድር እንዲካሔድ ከኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ጋር በመተባባር ያዘጋጁት አቶ ቢኒያም ነገሱን ከዚህ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የልፋታቸውን ፍሬ እንዲመለከቱ ጠንክረን እንሰራለን ብሏል፡፡

ውድድሩን ሶተኛ በመሆን ያጠናቀቀው የድሬዳዋ ከነማ ብስክሌት ክለብ ተወዳዳሪው አክረም ከድር ነው ፡፡

አክረም በውድድሩ ማብቂያ ላይ በሰጠው አስተያየትም ውድድሩን በበላይነት ለማጠናቀቅ ወስኖ መጀመሩን ያወሳ ሲሆን በተለይም በውድድሩ የአስተዳደሩ ከንቲባ ስፖርቱ እንዲጠናከር የድሬዳዋ ከነማ ብስክሌት ቡድን ዘመናዊ ሳይክሎችን በመግዛትና በመደገፍ እያደረጉት ያለውን አስተዋጾ የሚያስመሰግናቸው መሆኑን ገልጾ ፣ ውድድሩን አጅበው ተጫዋቾችን ማበረታታቸው ደግሞ እኛም የተሸለ ውጤት እንድናስመዘግብ ብርታትና ሞራል ሆኖናል ነው ያለው ፡፡

ታህሳስ 29 / 2017 ዓ/ም በተካሔደው በሁለተኛው ዙር በ29 ዙሮች 100ኪ/ሜትር በሸፈነው መነሻና መድረሻውን ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት አድርጎ በተካሔደው ውድድር በቡድን ወልዋሎ አዲግራት አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ የብስክሌት ክለብ በቡድን 7፡49 ፡15፡51 ሰዓት ድምር ውጤት አንደኛ ፣ ድሬዳዋ ከነማ 7፡49፡18፡51 በሆነ ድምር የሰዓት ውጤት ሁለተኛ ሲሆን ድሬዳዋ ቶቶ የብስክሌት ክለብ 7፡50፡30፡51 ድምር የሰዓት ውጤት ሶስተኛ ሆነዋል፡፡ ድሬዳዋ ፖሊስ ብስክሌት ክለብ በ 02 ሴኮንድ ዘግይቶ 4ኛ፣አዲስ አበባ ብስክሌት ክለብ በ013 ሴኮንድ ልዩነት 5ኛ ሲሆን የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የብስክሌት ክለብ 7፡57፡18፡73 በሆነ ድምር የሰዓት ውጤት 6ኛ ሆነዋል ፡፡

100ኪ/ሜትር የሚሸፍነውን የ29 ዙሮች ውድድር የወልዋሎ አዲግራት አዲስ መድሃኒት ፋብሪካ የብስክሌት ክለብ ተወዳዳሪው ኃለመለኮት ወልደ አብእዝጊ በ2፡35፡59 ፣የድሬዳዋ ቶቶ ብስክሌት ክለቡ አሚር ጃፋር 2፡36፡01 ፣ የድሬዳዋ ከነማ ብስክሌት ክለብ ተወዳዳሪው አክረም ከድር በ2፡36፡02 ሰአት ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡

ከታህሳስ 26 እስከ ጥር 4 በሚካሔደው ድሬ ሀሪፍ አገራቀፍ የብሰድክሌት ሻምፒዮና ውድድር ቀጣይ ጫወታ በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና አካባቢ የፊታችን ሃሙስ የሰዓት የግል ውድድር የሚካሔድበት ሲሆን እሁድ በከዚራ የፍጻሜ ውድድር የሚካሔድ መሆኑን የወጣው የውድድሩ መርሃ ግብር ያሳያል ፡፡

በዳንኤል አማረ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *