አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የገቢ መጠኑን በተሻለ ደረጃ ማሳደጉን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል።

ግምገማው ከዚህ በፊት በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ገበያ ማዕከላት፣ ማምረቻዎችን ወርክ ሾፕ መስክ ምልከታን ግብረ መልስ ያካተተ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው አባላትም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎችን አያይዘው ሠንዝረዋል።

አነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን አህመድ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚደረግላቸው ክትትልና ድጋፍ እንደጠቀማቸው ገልጸው ይህም ገቢያቸው ከማሳደግ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ አንደነበረው አመልክተዋል።

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዓይናለም ተዘራ በሠጡት የማጠቃለያ ሃሳብ ኮርፖሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው የስራ ዘርፎች በርካታ እንደመሆናቸው የተገኙ ውጤቶች አበረታች ናቸው ሲሉ ጠቅሰዋል።

ወ/ሮ አይናለም አያይዘውም ገቢን የበለጠ ለማሳደግ ወጪ አስተዳደር ላይ የታዩ ክፍተቶችን ኮርፖሬሽኑ እንዲያሻሽል አቅጣጫ ሠጥተዋል።

Dire tv

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *