January 13, 2025
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ሽኝት አደረጉ
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼህ መሃሙድ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ሽኝት አድርገዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ “በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለው” ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 ዓ.ም 2ተኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ዛሬ ተካሄደ።
”ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ የተካሄደው መድረክ በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ አባላት የተገኙበት መድረክ ተካሂዷል ። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙክታር እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት በመሠረታዊ ድርጅት የታቀዱ እቅዶችን ከግብ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀዋል። በተለይም አዳዲስ አባላትን ከማፍራት አንፃርና በሰው ተኮር ስራዎች ላይ…
የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዝዳንቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ “የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ” ብለዋል፡፡
አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የገቢ መጠኑን በተሻለ ደረጃ ማሳደጉን አስታወቀ።
የኮርፖሬሽኑ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል። ግምገማው ከዚህ በፊት በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ገበያ ማዕከላት፣ ማምረቻዎችን ወርክ ሾፕ መስክ ምልከታን ግብረ መልስ ያካተተ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው አባላትም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎችን አያይዘው ሠንዝረዋል። አነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) መርቀው ከፍተዋል።
ይኽ ተግባር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በማዘመን ረገድ ዐቢይ ርምጃ ነው። ESX ለዘርፉ ግልፅነትን የተላበሰ የገበያ ስፍራ ይፈጥራል። በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጥላ ሥርም በኢንቨስትመንት ለሚመራ እድገት በር ይከፍታል። በመንግሥትም በግልም ዘርፎች የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት የቁጠባ እንቅስቃሴን ማሳደግን ብሎም ኢንቬስተሮችን መጠበቅን ታላሚ አድርጎ ተነስቷል። ESX በሶስት የገበያ ክፍሎች ላይ ይሰራል። እነዚህም ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግሥት እና…


