የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 ዓ.ም 2ተኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ዛሬ ተካሄደ።

”ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ የተካሄደው መድረክ በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ አባላት የተገኙበት መድረክ ተካሂዷል ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙክታር እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት በመሠረታዊ ድርጅት የታቀዱ እቅዶችን ከግብ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀዋል።

በተለይም አዳዲስ አባላትን ከማፍራት አንፃርና በሰው ተኮር ስራዎች ላይ በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ገልፀው የአባላት የግንኙነት አግባብና አባላትን ማጥራት ስራ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ አመት እና የኦዲት ኮሚሽን የፓርቲው እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል ።

አዲስ አባላትን የማፅደቅና በማዕከል በሚደረግ የማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ የሚሳተፉ አባላትም ምርጫ ተካሂዷል።

በንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት አራት ህዋሳት ሲኖሩ በአጠቃላይ 127 የፓርቲ አባላት እንደሚገኙ በሰነዱ ተጠቅሷል ።

”ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የማጠቃለያ ኮንፍረንስ ላይ የቀጣይ ስድስት ወራት በትኩረት የሚሰራባቸውን ስራዎች ከቃል ወደ ተግባር የሚለወጡበትና አባላት ማፍራት እና ማጥራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተጠቅሷል ።

በመድረኩ ግንባር ቀደም አባላት የተመረጡ ሲሆን አዲስ እጩ አባላት ወደ ፓርቲው የተቀላቀሉበትና በቀሪ ወራት በተለይም በአስተዳደሩ በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ላይ አባሉ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ አቶ አብዲ ሙክታር በማጠቃለያ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *