የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ የሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኢፍቱ አህመድ ብልፅግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ የሴቶችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ከማረጋገጥ አንጻር በሁሉም መስክ በኢኮኖሚ በማህበራዊ ፖለቲካዊና በመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሴቶች እንዲሳተፉ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደራጅተው እንዲንቀሳቀሱ እና ግንባር ቀደም ሆነው ለሌሎች ሴቶችን ማሰለፍ እንዲችሉ የብልጽግና ፖርቲ ሴቶች ሊግ ይሰራል ብለዋል ።
በበጀት አመቱ የብልጽግና ፓርቲ በርካታ መደበኛና ወቅታዊ የንቅናቄ ተግባራትን ማከናወን መቻሉ የተገለፀ ሲሆን የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ የሚያጠናክሩ ለተልዕኮ ዝግጁ የሚያደርጉ ፣ ከማዕከል የወረዱ የተለያዩ ሰነዶች ወደታች ወርደው አባላት በተለያዩ የውይይት አዉዶች ግንዛቤ ያገኙበት ፣ የሊጉ የጉባኤ ውሳኔዎች አቅጣጫዎች ወደ ተግባር እንዲገቡ የተደረገበት ሲሆን በተለይም የአረንጓዴ አሻራ፣ በህዳሴ ግድብ ቦንድ ግዢ፣ የሌማት ቱርፋት ንቅናቄና የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሌሎችንም የመደበኛ ተግባራት በአጠቃላይ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ተረድቶ ፈጥኖ ተልዕኮዎችን በማዉረድ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሊጉ መዋቅር ግንባር ቀደም ሁኖ ደጋፊ ሴቶችንም ወደ ንቅናቄ በማስገባት በርካታ ስራዎች መከናወናቸው በመድረኩ ተመልክቷል ።


