በድሬዳዋ አስተዳደር ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተሰሩ ጠንካራ ስራዎች ነዋሪው ለረጅም ዓመታት ሲያማርር እና ሲያነሳቸው የነበሩትን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት እንደተቻለ ተገለፀ።
በድሬዳዋ አስተዳደር “ከቃል እስከ ባህል” በሚል የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የቅድመ ጉባኤ ማጠቃለያ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል እሳቤ የብልፅግና ፓርቲ ለህዝብ የገባውን ቃል በተጨባጭ ከመተግበር ባለፈ የኢትዮጵያን ህልም እውን ለማድረግ የህዝብ ፍላጎትና ስሜትን በመረዳት…


