የብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረ ወዲህ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ድሎች መመዝገባቸው ተገለፀ::

ከቃል እስከ ባህል” በሚል እሳቤ ” የብልፅግና ፓርቲ 2ተኛ መደበኛ የቅድመ ጉባኤ ማጠቃላያ ኮንፍረንስ በድሬዳዋ ተካሄደ።

በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ብልጽግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊና አሰባሳቢ የሆነ፣ ኢትዮጵያዊያን ያለ ብሄር፣ ህይማኖት ወይም ሌላ የማንነት ገደብ የሚደራጁበት፣ የሚሳተፉበትና ለሀገራቸው ብልፅግና የድርሻቸውን የሚወጡበት አንድ ወጥ ህብረ ብሄራዊ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት አምስት አመታት በዓለም ከሚገኙ ግዙፍ ፓርቲዎች አንዱ ለመሆን መቻሉን ገልፀዋል።

ፓርቲው ለነዋሪው የገባውን ቃል በተግባር እያሳየ እንደሚገኝ አቶ ኢብራሂም ጠቁመው በቀጣይም ሰው ተኮር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመው፤ በቀጣም በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመላክተዋል።

የኮንፍረንሱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የብልጽግና ፓርቲ ሀገር መምራት ከጀመረ ወዲህ በሁሉም ዘርፍ በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ገልፀው እንደ ሀገር የተጀመረዉ የብልጽግና ጉዞ ግቡን እንዲመታም ከመቼዉም ጊዜው በበለጠ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አመላክተዋል።

በኤደን ሳሙኤል

ፎቶ:- አገኘሁ ሸዋረጋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *