የከተራ እና ጥምቀት በዓል በድምቀት ተከብሮ እንዲያልፍ ተገቢዉ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር ምእራፍ መሻገሩን ግብረ ሀይሉ ጨምሮ አስታዉቋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ሰብሳቢነት የሚመራዉ ድ/ዳ ፀጥታ ግብረሀይል በአሉን አስመልክቶ በአካሄደዉ የዉይይት መድረክ እዳስታወቀዉ በድ/ዳ እንደ አለፉት አመታት ሁሉ የጥምቀት በአል በደመቀና በአማረ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ተገቢዉ ዝግጅት መጠናቀቁን ነዉ ያስታወቀዉ ።
የጥምቀት በዓል ሐይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ቀደም ባሉ ቀናት ከእምነቱ አባቶችና የተለያዩ የማ/ብ ክፍሎች ጋር በቂ የዉይይት መድረኮች መካሄዳቸዉን የገለፀዉ የአስተዳደሩ የፀጥታ ግብረ ሀይል አሁን ላይ የበአል ስምሪቶች ተሰጥተዉ ወደ ተግባር ምእራፍ መሻገሩን ገልፆል።
የበአሉን አከባበር ሊያዉኩና ሊያስተጓጉሉ የሚችሉ የትኛዉንም አይነት እንቅስቃሴና ተግባር ፈፅሞ እንደ ማይታገስ ያስታወቀዉ የአስተዳደሩ የፀጥታ ግብረ ሀይል ለበአሉ ፍፁም ሰላማዊነት የፀጥታ ሀይሉ ከምንገዜዉም በላይ ዝግጁ ነዉ ብሏል ።
በአሉ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ መላዉ ህዝበ ምእመንና የአስተዳደሩ ነዋሪ እንደ ከእዚሂ ቀደሙ ሁሉ ለፀጥታ አካሉ ተገቢዉን ትብብርና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪዉን ያቀረበዉ የአስተዳደሩ የፀጥታ ግብረ ሀይል ከበአሉ ጋር ተያይዞ ከሀገሪቱ የፌደራል እና የቤተክርስቲያኗ ሰንደቃላማና አርማ ዉጪ ሌላ ምንም አይነት አርማና ሰንደቅ መያዝና መጠቀም የተከለከለ ና የማይቻል መሆኑን እንዲሁም የትኛዉንም አይነት የጦር መሳሪያና ስለታማ መሳሪያዎች ፣ፀብ ጫሪ ፁሁፍና መልእክቶች ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መጠቀም ፈፅሞ የማይፈቀድ መሆኑን የጋራ ግብረ-ሀይሉ ጨምሮ አስታዉቋል።
ምንጭ፡ የፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ


