የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከሰላሳ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል መፈጠሩን አስታወቀ::

በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለ45 ቀናት ያሰለጠናቸውን 31 የኢንደስትሪ ስራ ላይ ደህንነት ተቆጣጣሪ ባለሞያዎችን በድምቀት አስመርቋል ፡፡

በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት ከሰላሳ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት የስራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ገልፀዋል፡፡

የስራ ዕድል ፈላጊዎች ወደ ስራ ከመሰማራታቸው በፊት ከሚሰሩት ስራ ጋር ተያያዥ የሆኑ አጫጭርና መካከለኛ ስልጠናዎችን መውሰዳቸውንና፤ በስራ ላይ በሚቆዩበት ጊዜም በጥናት ላይ የተደገፈ ክትትልና የስራ ላይ ስልጠና በቴክኒክ ኮሌጆች አማከኝነት እየተሰጠ መሆኑንም አቶ ሮቤል አያይዘው ተናግረዋል።

በመጨረሻም አቶ ሮቤል በድሬዳዋ የኢንደስትሪ ስራ ላይ የደህንነት ደረጃን በማስጠበቅ ረገድ የሚኖራችሁን ከፍ ያለ ሚና በአግባቡ መወጣት ይገባቹሀል ሲሉ ለተመራቂዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ተመራቂዎች በበኩላቸው በስጠና ቆይታቸው ባገኙት እውቀት ማህበረሰቡን ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በከበደ ካሳ

ፎቶ ፡- ቴዎድሮስ ልዑልሰገድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *