የከተራና የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተከብሮ እንዲያልፍ ከሃይማኖት አባቶች ጋር የቅድመ ዝግጅት የውይይት መድረክ ተካሄደ።

በውይይት መድረኩ የሀይማኖት አባቶች የድ/ዳ ፖሊስና ኮሚሽነርን ጨምሮ የሰላምና የፀጥታ አመራሮች ተገኝተዋል።

የከተራና ጥምቀት በአልን አሰመልክቱ የተካሄደዉን የዉይይት መድረክ የመሩት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዠ ኮሚሽነር አለሙ መግራ እንደቸናገሩት ” ዛሬ ላይ በድሬደዋ ማረጋገጥ በተቻለዉ ሰላምና የነዋሪዎቿ አንድነት ከሀገራችን አልፎ ከሌሎችም ክፍለ አለማት ጭምር ሀይማኖታዊም ሆነ ለሌሎች ክብረበአላትን ለማክበር እንግዶች የሚመርጧት ከተማ ለመሆን ችላለች ያሉ ሲሆን ይህንኑ አስጠብቆ በዘንድሮዉ የከተራና ጥምቀት በአልም አጉልቶ ማሳየት ይገባል ነዉ ያሉት።

ለእዚህም አስተዳደሩ ፖሊስና ሌሎችም የፀጥታ ተቋማት ከምንግዜዉም በላይ ለበአሉ ሰላማዊነት መሪ የበአል የፀጥታ እቅድ በማዘጋጀት ተገቢዉ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ መላዉ የእምነቱ ተከታይና የአስተዳደሩ ነዋሪም እንደ ከእዚሂ ቀደሙ ሁሉ በአሉን በፍቅር በአንድነት በማክበር ፍፁም ሰላሚ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩልን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።

በእዚሁ የጋራ ዉይይት መድረክ የተገኙት የድ/ዳ ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉ/ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ አብደላ በከር የከተራ ጥምቀት በዓል በዩኔስኮ የተመዘገበ በዓል ጭምር እንደ መሆኑ አብሮነታችንና ወንድማማችነታችንን ብሎም የሀገራችንን ገፅታ ከፍ አድርገን የምናሳይበት ሊሆን ይገባል ነዉ ያሉት ።ለእዚህም ሁሉም አካል የድርሻዉን ሊወጣ እንደሚገባ በመግለፅ ።

በዉይይት መድረኩ የተገኙ የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው የከተራና የጥምቀት በዓል ሀይማኖታዊ ስርአቱን ጠብቆ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሮ እንዲያልፍ ቤተክርስቲያኗ ተገቢዉን ቅደመ ዝግጅት ያደረገች ስለመሆኑ ገልፀዉ ከበአሉ አከባበር ጋር ተያይዞ በየ አድባራቱ ትምህሮቶችና ገለፃዎች መደረጋቸዉን ነዉ የተናገሩት።

የጥምቀት በአል ስናከብር ከቤተክርስቲያኗ አባቶችና ከፀጥታ ሀይሉ የሚተላለፉ መልእክቶች ተቀብሎ በመተግበር ጭምር ሊሆን ይገባልም ያሉት የእምነቱ አባቶች በድሬደዋ ለአለዉ ሰላምና የእምነት በአላት በማረና በደመቀ መልኩ እንዲከበሩ በማስቻል እረገድ የአስተዳደሩን ከንቲባ ጨምሮ ለድ/ዳ ፖሊስና ለሌሎችም የአስተዳደሩና የፌደራል የፀጥታ ተቋማት ምስጋናቸዉንም አቅርበዋል።

የከተራ ጥምቀት በአል በአል በድሬዳዋ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ ተከብሮ እንዲያልፍ የፀጥታ ሀይሉ ቅድመ ዝግጅቶቹን አጠናቆ አሁን ላይ ወደ ተግባር ምእራፍ መሻገሩን የወጣዉ የበአሉ መሪ የፀጥታ እቅድ የሚያመላክት ሲሆን መጪዉ የጥምቀት በአልን በድሬዳዋ ለማክበርና ለመታደም ከሀገሪቱና ከሌሎች ክፍለ አለማት ጎብኝዎችና እንግዶች ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በእዚሁ የጋራ የዉይይት መድረክ የድ/ዳ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ጉሌድ ድርዬን ጨምሮ የድ/ዳ ሀገረ ስብከትና የደብር አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የድ/ዳ/ፍትህና ፀጥታ ቢሮ አመራሮች ተገኝተዋል።

ምንጭ፡ የፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *