በድሬዳዋ አስተዳደር በልዩ ድምቀት እየተከበረ ባለው የጥምቀት በአል ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንደዚሁም በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የአስተዳደሩ አመራሮች ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር በመሆን ታቦታቱ ከማደሪያቸው ወደ አድባራቱ የሚያደርጉትን ጉዞ አጅበዋል፡፡
ታቦታቱን በማጀብ ለሚጓዘው ምእመን ፣የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምህራንና የእምነቱ ተከታዮች የየወረዳዎቹ አመራሮች የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር ያዘጋጁዋቸውን ጣፋጭ ምግቦችና የታሸገ ውሃ በመስጠት የድሬዳዋን መልክ አጉልተው እና አድምቀው ሲያንጸባርቁና የበአሉ ሌላ ተጨማሪ ውበት ሆነው ታይተዋል፡፡


