የድሬደዋ ፀጥታ ግብረ ሀይል እንዳስታወቀዉ ሁሉም ታቦታት ከጥምቀተ ባህር ወደ መንበረ ክብራቸው በፍፁም ሰላምና ድምቀት መመለሳቸውን ገልፆ ለበዓሉ ፍፁም ሰላማዊነትም ምስጋናውን አቅርቧል::
#DGC | 2017 ዓ.ም
በታላቅ ድምቀት በአደባባይ የሚከበረው የጥምቀትና ከተራ በአል ፍፁም ሰላማዊነት አስቀድሞ የበአል ፀጥታ እቅድ በማውጣት ወደ ስራ መግባቱን የገለፀው የአስተዳደሩ ፀጥታ ግብረ ሀይል በጥምቀት ሆነ በከተራ በአል ምንም አይነት የየወንጀል ተግባርም ሆነ የትራፊክ አደጋ ሳይከሰት በአሉ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ መከበሩን ነው ያስታወቀው::
ግብረ ሀይሉ ጨምሮ እንዳስታወቀው በድሬደዋ ካለፉት የለዉጥ አመታት ወዲሂ በአስተዳደሩ የሚከበሩ ሀይማኖታዊም ሆነ ህዝባዊ በአላት ብሎም በእለት ተእለት የህ/ብ እንቅስቃሴ የፀጥታ ችግር እንዳይከሰትና እንዳያጋጥም መላው ህ/ብን ባሳተፈ መልኩ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎችና ከአስተዳደሩ ጋር በሰራቸው የከተማዋንና የነዋሪዎቿን ሁለተናዊ ሰላም የማረጋገጥ ስራዎች ከፍተኛ ውጤቶችን ማምጣት አስችሏል ነው ያለው ::
የዛሬዉ የ2017 የጥምቀትና ከተራ በዓል ፍፁም ሰላማዊነትም የህዝባችንን ሰላም ወዳድነት፣አንድነት ወንድማዊ ፍቅርና በአብሮነት የመኖር እረጅም ግዜያትን ባህልና እሴት ይበልጥ ከፍ ባለ መልኩ የታየበትና ያረጋገጠበትም ጭምር ነው ብሏላ ግብረ ሀይሉ በመግለጫው ።
በድሬዳዋ የጥምቀትና ከተራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር ህዝበ ምእመኑ፣መላው የአስተዳደሩ ነዋሪ፣የፀጥታ ሀይሎችና ተቋማት፣አጋዥ የህ/ብ ክፍሎች ፣ የድ/ዳ አስተዳደርና የፀጥታ ምክር ቤት እንዲሁም መላ የሰራዊቱና የፀጥታ አካላት ለነበረቻው ተኪ የለሽ ሚናና ከፍ ያለ አስተዋፆ የድሬደዋ ፀጥታ ግብረ ሀይል የላቅ ምስጋናውንም አቅርቧል።
ምንጭ፡ የፍትህ ፀጥታንል ህግ ጉዳዮች ቢሮ


