ድሬ ፖሊስ Ill ጥር 11 .2017 ዓ.ም

ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የህዝብ ሀብትን መዝብሯል ተብሎ የተጠረጠረን ግለስብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርምራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ ።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የመንግስት ሀብትን አለአግባብ ከህግና አሰራር ውጭ በሆነ መንገድ ምዝበራ ፈፅሟል ብሎ በተጠረጥረው የድሬዳዋ ከነማ ስፖርት ክለብ የቦክስ አሰልጣኝ የሆነው ኤፍሬም ነጋሽ የተባለ ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በመጣራት ላይ መሆኑን ገልጿል ፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጋር በጥምር እያጣሩት በሚገኙትና በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ በቁጥጥር የሚገኘው የቦክስ አሰልጣኝ ተጠርጣሪ ኤፍሬም ነጋሽ በአሰልጣኝነት የነበረውን ኃላፊነት ተጠቅሞ ከክለቡ እውቅና የሌለው ማህተምን በማሰራት በስፖርቱ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ ላልነበራቸው ግለሰቦች ከመንግስት ካዝና በተደጋጋሚ ተገቢ ያልሆኑ ክፍያዎች እንዲፈፀሙ በማድረግና የወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን አንዲሁም ከክለቡ ለቦክስ ተወዳዳሪዎች የሚሰጠውን ስፖርታዊ ትጥቆችን ለተወዳዳሪዎች ከመስጠት ይልቅ ለግል ጥቅም በማዋልና ከዚሁ ከተማ የተቀጠሩ ቦክስ ተወዳዳሪዎችን ሀሰተኛ ማስረጃዎችን በማዘጋጀት ከሌላ አካበቢ የተቀጠሩ በማስመሰል ከፍተኛ የደሞዝ ክፍያን እንዲፈፀም በማድረግና በሌሎችም የሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርምራ ዋና መምሪያ እየገለፀ ፡፡

ነገር ግን ሰሞኑን በጉዳዩ ዙሪያ በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ የሚሰራጩ አንዳንድ መረጃዎችና ዘገባዎች ከእዉነታ የራቁና መሰረተ ቢስ መሆኑን ለህበረተሰቡ እየገለፀን በቀጣይ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃ ምርምራው ሂደት እንደተጠናቀቀ የምናሳውቅ ሲሆን እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ አስፈላጊ መረጃዎችን ማግኘት እየተቻለ የአስተዳደሩ ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርምራ የሚያጣራበትን ሂደት በማዛባት ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ዜናዎች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ህብረተሰቡ እንዲገነዘብ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና መምሪያ ጨምሮ ይገልፃል ።

ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *