የግምገማ መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፓርቲው የመጀመሪያ ታሪካዊ ጉባኤውን ካካሄደ በኋላ አሁን ላይ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን ለማድረግ በዝግጅት ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ የተሰሩ ስራዎች እንደ አስተዳደር ተገምግመው ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ለማስቀል ብሎም ደካማ ጎኖች ላይ አተኩሮ ለመስራትም የዛሬው መድረክ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ኢብራሂም አያይዘውም ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር በመሆኑም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች እንዲሁም የሌማት ቱሩፋትና የበጎ ፍቃድ ስራዎች እንዴት ተሰሩ የሚለው እንደሚገመገም እንዲሁም በህዝቡ የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደርና ጥያቄዎች እንደሚፈተሹ አመላክተዋል።
ባጠቃላይ በግምገማው ማህበረሰቡ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰሩ ስራዎች ላይ፤ በተጨማሪም የዝግጅት ምእራፍ ስራዎች እንዴት ተከናወኑ እንዲሁም ደግሞ በትግበራ ምእራፍ በተለይ አመራሩ በህዝብ ንቅናቄ የተሰሩት ስራዎች እንዴት ተፈፀሙ የሚለው ላይ ውይይት እንደሚደረግ አቶ ኢብራሂም ተናግረዋል።
በኤደን ሳሙኤል
ፎቶ:- ሰላም አበበ


