የኢንደስትሪ ማእከልነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ስራዎችን በማገዝ ረግድ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑንን የአስተዳደሩ መሬት ልማት ማንጅመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክርቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡

በአስተዳደሩ እየተካሄደ በሚገኘው የኮሪደር ልማት የመልካ ጀብዱ የኮሪደር ልማት፥ የነፃ የንግድ ቀጠና ፣ የምድር ባቡር እና የደረቅ ወድቡን በመኪና ትራንስፖርት በማሳለጥ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡

ለዚህ ኮሪደር ግንባታ ለተነሺዎች ምትክ ቦታ በመስጠት እና ቦታውን ለልማት በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ የ6 ወራት የቢሮውን አፈፃፀም በተመለከተ ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የከተማ ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የገለፁት የቢሮው ሀላፊ ኢንጂነር ሳጅድ አልዬ ናቸው፡፡

ከተማዋን የኢንዱስትሪ መናኸሪያ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት 600 ሄክታር መሬትን ለልማት ዝግጁ የማድረግ ስራ መከናወኑን የገለፁት ሀላፊው የአልሚዎችን የማስፋፊያ ጥያቄዎችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በኮሪደር ልማት ለሚነሱ ነዋሪዎች ቦታ በማዘጋጀት መንገዶችን በመክፈት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራም ይገኛል ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ቤዛ ዳምጠው በበኩላቸው ቢሮው የተሰጡትን ግብረ መልሶች በማረም በኩል ጥሩ አፈፃፀም ማሳየቱን ገልፀው የተገልጋይ እርካታን በአግባቡ ለማረጋገጥ የቢሮው የመዋቅር ጥናት ተግባራዊ መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡

ከተማዋ ያላትን የኢንቨስትመንት ተመራጭነት ለማሳደግና ተወዳዳሪ ለማድረግ የኮሪደር ልማት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠልም አለበት ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *