የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለተከታታይ ቀናት ምልከታ ያደረገባቸውን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮን የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያ 6ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና ግብረ መልስ ሰጥቷል

የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋም የሆኑት የገቢዎች ባለስልጣን አመራሮች በተገኙበት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ተገምግሟል ።

ቋሚ ኮሚቴው የመጀመሪያ 6 ወራት የተቋማት እቅድ አፈጻጸም ለመገምገም በተዘጋጀው ቼክ-ሊስት መሰረት ከአሁን በፊት ለቢሮው የተሰጡ ግብረ_መልሶች ፣የመደበኛ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የፋይናንስና ንብረት አያያዝ እና አስተዳደደር፣ የ6ወር የገቢ እቅድ አፈፃፀም የማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት የተሰሩ ስራዎችና ቅንጅታዊ አሰራሮችን ጨምሮ ሌሎች ከቋሚ ኮሚቴ አባላቶች የተነሱ ጥያቄዎች ላይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮው ሀላፊ የተከበሩ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ አያይዘው እንደተናገሩት በየጊዜው በቋሚ ኮሚቴው የክትትል እና ቁጥጥር ስራው የሚሰጡ ግብረመልሶች ለቢሮው አጋዥ መሆኑን ገልፀዋል።

የገቢዎች ባለስልጣን ስራአስኪያጅ አቶ አብዱሰላም መሀመድ በበኩላቸው የአስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ በ6ወር እቅድ አፈፃፀም በርካታ ስራዎች መሰራታቸውንና በቀጣይ ለገቢ አሰባሰቡ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ቢሮው እና የገቢዎች ባለስልጣን የ2017ዓ/ም የመጀመሪያ 6ወር የእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ላይ በጥንካሬ እና ውስንነት የተወያዩባቸው ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤ ከተያዘ በኋላ የመውጫ ግብረመልስ ተሰጥቷል፡፡

በመጨረሻም ከባለፈው አመት 6ወር አፈፃፀም ጋር በንፅፅር ሲታይ የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እንዲሁም የአስተዳደሩን ገቢ ለማሳደግ የለያዩ አማራጮችን በመጠቀም እየተከናወኑ ያሉ በርካታ ዝርዝር ተግባራት መከናወናቸውን በጥንካሬ የተገመገመ ሲሆን በውስንነት የተነሱ ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ቢሮው ከሚመለከተው ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ንግድና ኢንደስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አይናለም ተዘራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *